
ሰቆጣ፡ ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ በሴቭ ዘችልድረንና በቅሸነ ቲያትርና ፕሮዳክሽን ትብብር የተዘጋጀው “እኔ እራሴንና ሀገሬን ከሱስ እታደጋለሁ” በሚል መሪ መልእክት 5ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሩጫ እየተካሄደ ነው።
በውድድሩም ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በፕሮግራሙም የሴቭ ዘችልድረን ዳይሬክተርን ጨምሮ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!