ከ5 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የሩጫ ውድድር በሰቆጣ ከተማ ተካሄደ።

27

ሰቆጣ፡ ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ በሴቭ ዘችልድረንና በቅሸነ ቲያትርና ፕሮዳክሽን ትብብር የተዘጋጀው “እኔ እራሴንና ሀገሬን ከሱስ እታደጋለሁ” በሚል መሪ መልእክት 5ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሩጫ ተካሂዷል።

በውድድሩም ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።

የሩጫ ውድድሩ በሴቭ ዘችልድረንና በቅሸነ ቲያትርና ፕሮዳክሽን ትብብር የተዘጋጀ ነው።

በፕሮግራሙም የሴቭ ዘ ችልድረን ዳይሬክተርን ጨምሮ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።

የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ተወካይ ከንቲባ እና የባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አደራጀው ቀለመወርቅ በመክፈቻው ላይ ወጣቱ ከሱሰኝነት በመላቀቅ በስፖርት ጤንነቱን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ይህ አይነቱ ፕሮግራም ለወጣቱ የሚሰጠው ፋይዳ ላቅ ያለ በመኾኑ ይህን ያዘጋጁ አካላት ምሥጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ቀጣይም እንዲህ አይነት ፕሮግራም ለሚያዘጋጁ ሁሉ ከተማ አሥተዳደሩ ከጎናችሁ እንደኾነ አስረድተዋል።

የሩጫው አሸናፊ ወጣት ዘርፌ ካሣም “ይህ ዓይነቱ ሩጫ ለኛ ለተስፈኛ አትሌቶች አስፈላጊ ነው ስላሸነፍኩም ደስተኛ ነኝ” ብላለች።

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ቦርከና መቀነቷ፣ ሐረጎ ጉልላቷ”
Next articleበሰቆጣ ከተማ ሱሰኝነትን የሚጠየፍ ትውልድ ለመገንባት ያለመ የሩጫ ውድድር ተካሄደ።