የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

78

ባሕር ዳር: ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “አዲስ ምዕራፍ እና አዲስ ተስፋ ለአዲስ ክልል” በሚል መሪ ሃሳብ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ነው፡፡

በሕብረ ብሔራዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንነትን መሠረት ያደረገ የራስ አሥተዳደርን የመመሥረት ሂደት ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎችን ይፈታል፡፡

መንግሥት ማዕከላዊ አስተሳሰብን በመያዝ በጋራ እና በሕብረት ለመቆም የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖር ላደረገው ጥረት ምስጋና ያቀረቡት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር እንደሻው ጣሰው ናቸው፡፡ ርእሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው የሕዝብን ፍላጎት እና ጥያቄ በትጋት እና በቅንነት የመለሱትን ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ በመቆም እና በመሥራት አብረን ለኢትዮጵያ መጻዒ እጣ ፋንታ እንተጋለን ነው ያሉት፡፡ አንድ እና ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት እንዲኖር ክልሉ ከፌደራል እና ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ ተቀራርቦ ይሠራል ብለዋል፡፡

ለአዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሌሎች ክልሎች እና የፌደራል መንግሥት ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ርእሰ መሥተዳድር እንደሻው ጣሰው ጠይቀዋል፡፡

በታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምስረታ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአፋር ክልል የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎበኙ::