
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምስረታ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ-ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች ፣ ከንቲባዎችና ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል።
“የጋራ እሴቶቻችንና ጥቅሞቻችንን በማስተባበር ጠንካራ ክልል እንገነባለን ፤ በአዲስ ምእራፍ የጋራ ትጋት ለጋራ ስኬት” የሚሉና ሌሎች የክልሉን አንድነት የሚያንፀባርቁ መልእክቶችም በአደባባዮች እየተስተጋቡ ይገኛሉ።
ተጨማሪ መረጃዎችን እናደርሳለን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!