
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመኾን የልማት ሥራዎችን ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ምርት ሥራን ለማስጀመር አፋር ክልል ተገኝተዋል::
በዱብቲ ወረዳ ኅብረተሰቡ በ8ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ተዘጋጅቷል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በያዝነው ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ3 ሚሊዮን ሔክታር ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት አቅደናል ብለዋል ::
በዋነኝነት በአርብቶ አደርነት የሚታወቀው እና በግብርና ግብዓቶች የቀዳሚ ድጋፍ መዳረሻ ያልሆነው የአፋር ክልል በአኹኑ ወቅት በሀገር አቀፉ የግብርና ምርታማነት ላይ በስንዴ በጥጥ በሙዝ ምርት አስተዋፅኦው እጅግ ከፍ እያለ መጥቷል:: መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!