ሀዲያ ነፈራ ደምቋል።

53

አዲስ አበባ: ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምስረታ በነገው ዕለት በይፋ ይካሄዳል። የሀድያ ማኅበረሰብ ልዩ ልዩ በዓላት ማክበሪያ የኾነው ቦታ “ሀዲያ ነፈራ” ለነገው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ መርሀ ግብር ደምቆ ተውቧል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምክር ቤቱን ውሳኔ ካገኘ በኋላ አቶ እንደሻው ጣሰውን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ነው። በነገው ዕለትም ይፋዊ የመንግስት ምስረታ ሥነ ሥርዓቱ በይፋ ይከበራል።

በሥነ ሥርዓቱም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቺርቤዋ ትክምቲ 15 ጌር 2016 ም.አሜታ
Next article“በመስኖ ልማት ከ40 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል” ግብርና ቢሮ