
ባሕር ዳር: ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ከሦስት ዓመታት በኃላ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ለሚያዘጋጁት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሕዳር ወር ላይ ጨዋታውን ማድረግ ይጀምራል። በምድብ አንድ የተመደበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ሕዳር አምስት ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር ይጫወታል።ከሦስት ቀናት በኃላ ደግሞ ቡርኪናፋሶን ይገጥማሉ።
እነዚህን ጨዋታዎች በሜዳዋ ማድረግ የነበረባት ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ መስፈርቶችን የሚያሟላ ሜዳ የሌላት በመኾኑ በሞሮኮ እንደምታከናውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
ካዛብላንካ የሚገኘው የመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ደግሞ ሁለቱን ጨዋታዎች እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!