
ባሕር ዳር: ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ማንቸስተር ዩናይትድ ዴቪድ ደሃያን መልሶ ለማስፈረም ተቃርቧል ተብሏል።
ደይሊ ሜይል የዜና ምንጭ እንዳስነበበው ማንቸስተር ዩናይትዶች ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ መልሰው ለማስፈረም የፈለጉት ካሜሮናዊው ግብ ጠባቂ አንድሪ ኦናናን በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ስለሚያጡት ነው።
እንደዘገባው ከኾነም ዩናይትዶች በሁለተኛ እና ሦስተኛ ግብ ጠባቂዎቻቸው እምነት የላቸውም። እናም ደሃያን ወደክለባቸው መልሰው የኦናናን የቀዳሚነት ቦታ ለመስጠት ወስነዋል።
ዴቪድ ደሃያ ከወራት በፊት ማንቸስተር ዩናይትድ መልቀቁ ይታወሳል። ኮንትራቱን ለማራዘም በክለቡ የቀረበለትን የደሞዝ ቀንስ ጥያቄ አለመቀበሉን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ለአሠልጣኝ ቴንሃግ የጨዋታ ፍልስፍና አይመችም ተብሎ ተገፍቶ ከኦልትራፎርድ መውጣቱን ያተቱ የወሬ ምንጮች በረካታ ነበሩ።
ስፔናዊ ግብ ጠባቂ በዩናትድ ቤት በርካታ ዓመታትን ያሳለፈ ሲኾን እንደ ቡድን ከዩናይትድ ጋር በርከት ያሉ ድሎችን ሲያስመዘግብ ፤በግልም ብዙ ክብሮችን አሸንፏል።
ዘጋቢ፡- አስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!