
ባሕር ዳር: ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ17ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በደቡብ ሱዳን በተሠማራበት የግዳጅ ቀጣና 116ኛውን የሠራዊት ቀን “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ አክብሯል።
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ጠንካራ ሠራዊት የነበራት፣ ከውስጥም ኾነ ከውጭ የሚነሱባትን ወራሪዎች በሠራዊቷ የጀግንነት ተጋድሎ እየመከተችና እያሸነፈች የመጣች ሀገር መኾኗን በክብረ በዓሉ ወቅት ተመላክቷል።
በዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ረገድ እስከ አሁን በርካታ የሠራዊት አባላትን በማሰማራት ግዳጁን በድልና በጥሩ ዲስፒሊን እየፈጸመ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ንግግር ያደረጉት የሞተራይዝድ ሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ ካሳዬ ኢትዮጵያ ልማቷንና እድገቷን ከማይፈልጉ የውጭ ወራሪዎች ራሷን አስከብራ የኖረችው ከጥንት ጀምሮ የተደራጀ፣ ጀግናና ፈተናዎችን በድል የሚሻገር ሠራዊት ስላላት መኾኑን አስገንዝበዋል።
ኮሎኔል ሞገስ “የአሁኑ ትውልዶች ከዘመኑ ጋር ዘምነን አኩሪ የጀግንነት ባህላችንን ማስጠበቅ ይገባናል” ሲሉም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!