“የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ መጥቷል” ደሳለኝ ጣሰው

41

ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ ወይይት እያካሄዱ ነው፡፡

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው የመድረኩ ዓላማ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመልሶ ማደራጀት አዲስ የተደራጀውን የፀጥታና የፖለቲካ መዋቅር በራሱ እንዲቆም ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ማኅበረሰቡ ውስጥ የደረሰውን ቀውስና ከላይ እስከ ታች የተናጋውን የክልሉን የፀጥታ መዋቅር በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲቆም ለማስቻል የጋራ አቅጣጫ እንደሚሰጥም ኀላፊው ተናግረዋል፡፡

አሁን ያለውን የጸጥታ ችግር በሰላም ለመፍታት የክልሉ መንግሥት የሰላም ጥሪ ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ኀላፊው አሁን ያለው ግጭት የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈታ ባለመኾኑ ከግጭት ውጭ በሃሳብ ብልጫና በውይይት መፍታት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ግጭቱ የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ልማት የሚያውክ እንጂ ጥያቄ አይመልስም ያሉት ኀላፊው ወደ ሰላም አማራጭ መግባት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ያለው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ከባለፉት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መኾኑን ያነሱት ኀላፊው አሁንም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉም አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እስመለዓለም ይሁን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አንድ ዓመት ራስን ለመለወጥ ከበቂ በላይ ነው” በአማራ ክልል ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ
Next article“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”