
ባሕር ዳር: ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምድብ ስድስት ላይ የተደለደሉ ቡድኖች የሚያደርጓቸው ጨዋታዎችም ይጠበቃሉ።
የሞት ምድብ በተሰኘው ምድብ ስድስት የእንግሊዙ ኒውካስትል ዩናይትድ ከጀርመኑ ቦሪሲያ ዶርትመንድ ፤ የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ከ ጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ይጫወታሉ።
ምድቡን በሁለት ጨዋታ አራት ነጥብ ያስመዘገበው ኒውካስትል ይመራዋል። ፒኤስጂ ሦስት ፣ ኤሲሚላን ሁለት እና ቦሪሲያ ዶርትመንድ አንድ ነጥብ ይዘዋል።
ምድብ ሰባትን በስድስት ነጥብ የሚመራው ማንቸስተር ሲቲ ወደ ስዊዘርላንድ ተጉዞ ያንግ ቦይስን ሲገጥም ፣ በዚሁ ምድብ የጀርመኑ አርቢ ሊፕዚንግ ከሰርቢያው ክርቪና ዚቭዚዳ ጋር ይጫወታል።
የስፔኑ ባርሴሎና ከዩክሬኑ ሻክታር ዶኔስክ ፣ የቤልጀሙ ሮያል አንቲሮፕ ከ ፖርቱጋሉ ፖርቶ የሚገናኙባቸው የምድብ ስምንት ጨዋታዎች ናቸው።
ምድብ አምስት ላይ የስኮትላንዱ ሴልቲክ የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድን ፣የኔዘርላንዱ ፌየኖርድ የጣሊያኑ ላዚዮን በሜዳቸው የሚገጥሙባቸው ጨዋታዎችም ዛሬ የሚካሄዱ ይኾናል።
እንደ ቢቢሲ መረጃ ፌየኖርድ ከላዚዩ እና ባርሴሎና ከሻክታር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ምሽት 1 ሰዓት ከ45 የሚካሄዱ ሲኾን ቀሪ ጨዋታዎች ደግሞ ምሽት 4 ሰዓት ይከናወናሉ።
ዘጋቢ፡- አስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!