
ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ለ7 የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ቦርዱ፦
1. ለፕሮፌሰር ዮናስ ጨቡዴ
2. ለፕሮፌሰር አህመድ ሙስጠፋ
3. ለፕሮፌሰር ኑርልኝ ተፈራ
4. ለፕሮፌሰር አምቢሳ ቀነዓ
5. ለፕሮፌሰር ፈቃዱ ጋሻው
6. ለፕሮፌሰር አበባው ይርጋ እና
7. ለፕሮፌሰር ታደሰ በሪሶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም ቦርዱ፦
1. ለፕሮፈሰር ሚሊያርድ ደርበው
2. ለፕሮፌሰር አታላይ ዓለም እና
3. ለፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ሰለሞን የኢሜሪተስ ፕሮፌሰርነት ደረጃ መስጠቱን ከዩኒቨርሲቲው ለአሚኮ የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!