በኮንስትራክሽ ኢንዱስትሪ ዙሪያ የሚሠሩ ጥናት እና ምርምሮች በዘርፉ ላሉ ችግሮች መዉጫ መንገድ እንደሚኾኑ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

61

አዲስ አበባ: ጥቅምት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችና በተሠሩ ጥናቶች ዙሪያ ዉይይት አካሂዷል።

በዉይይቱ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር ድኤታ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የኮንስትራክሽን ዘርፉ በርካታ የሰው ኀይልን የሚሸፍን ሲኾን ዘርፉ ለኢኮኖሚ የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።

ይህንን ዘርፍ በጥናትና ምርምር መደገፍ ለዘርፉ እድገት አስፈላጊ ነዉ መኾኑን አንሥተዋል።የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመት ኢንስቲትዩት ይህንን ተግባራዊ እንዲያደርግ ኀላፊነት እንደተሠጠዉ ጠቅሠዋል።

ጥናቶቹ በዘርፉ በሚሠማራዉ የሰዉ ኀይልና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ባለዉ ድርሻ ዙሪያ የተዘጋጁ መኾናቸዉ ተጠቅሷል።

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት ሞሉ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰዉ ኀይልና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ባለዉ ድርሻ ዙሪያ የሚደረጉ ዉይይቶች፣ ጥናት እና ምርምሮች ችግር ፈቺ እንደሚኾኑም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ለማ ጉዲሳ (ዶ.ር) በበኩላቸዉ የማኅበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ ጥናትና ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ ጠቅሠዉ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ የዚኹ አካል በመኾኑ በጥናትና ምርምር እንዲደገፍ በጋራ እንሠራለን ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዕሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ያለመ “ኔስት” የተባለ ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ ተጀመረ።
Next articleየአማራና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ምክክር አደረጉ።