
አዲስ አበባ: ጥቅምት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተሟላ የሠራዊት ቁመና እና አሠራር ተዘርግቶ የጦር ሠራዊት የተቋቋመበት 116ኛው የሠራዊት ቀን በድምቀት ይከበራል” ሲል መከላከያ ሚኒስቴ ገልጿል፡፡
በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት 12 አባላት ያሉት የመንግሥት ሠራዊት ሲቋቋም ፊታውራሪ ሃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የሠራዊቱ አለቃ ኾነው ተሾመዋል።
ይህ የኢትዮጵያ መደበኛ መንግሥታዊ ሠራዊት የተቋቋመበት 116ኛ ዓመት የሠራዊት ቀንም ጥቅምት 15/2016 ዓም የሠራዊት ቀን ተብሎ በድምቀት ይከበራል ተብሏል፡፡
ይህን ቀን ለማክበር እንደ ገፊ ምክንያት የኾነውም ሰላምን ለማስፈንና ከፍታ ለመስጠት፣ ለሠራዊቱ እውቅና ለመስጠት፣ ከሕዝብ ጋር ተገናኝቶ ቃሉን የሚያድስበት እንዲሁም ውትድርናን ለማሞገስ ታሳቢ ያደረገ እንደኾነም ነው የተብራራው፡፡
የበዓሉን ሁነት በማስመልከትም በመከላከያ ሚኒስቴር የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!