ኢትዮጵያውያን እጩ በኾኑበት የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ኬንያዊቷ አትሌት በሕዝብ ድምጽ እየመራች ነው።

42

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን በድል ላኮሩ አትሌቶች ቀላል ውለታ ብንውልስ?!

ባሕር ዳር: ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የዓለም አትሌቲክስ ተቋም የዓመቱ ምርጥ አትሌት እጩዎችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዓመቱ አስደናቂ አቋም ያሳዩ አትሌቶች በተካተቱበት የሴቶች ምርጥ እጬ ኢትዮጵያውያኑ ጉዳፍ ፀጋየ እና ትዕግስት አሰፋ ይገኙበታል።

አትሌት ጉዳፍ በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ለሀገሯ ወርቅ ማስገኘቷ ይታወሳል። ከወር በፊት ደግሞ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን አሻሽላለች።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የማራቶንን ክብረ ወሰን በደቂቃዎች በማሻሻል አስገራሚ ብቃት አሳይታለች።

የዓመቱ ምርጥ ሽልማትን ለማግኘት ከመስፈርቶቹ መካከል ፌስቡክ ላይ ብዙ ወዳጅ /like/ ማግኘት አንዱ ነው መኾኑ ተገልጿል።

የኬንያው ቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮምን ጨምሮ በርካታ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ተቋማት ለአትሌቶቻቸው ድምፅ እንዲሰጥ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም ውጤት አምጥቶ ኬኒያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን 69 ሺህ ላይክ አግኝታ እየመራች ነው።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋይ 18 ሺህ፣ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ደግሞ 15 ሺህ ላይክ አግኝተው እየተከተሉ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያኮሩንን አትሌቶች ብዙ ላይክ /like/ አግኝተው የውድድሩ አሸናፊ እንዲኾኑ የበኩላችንን በመወጣት ትንሹን ውለታ ልንውልላቸው እንችላለን።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ12ሺህ በላይ የሥራ ላይ ሠልጣኞችን ተቀብሎ እያሠለጠነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ፡፡
Next articleበሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?