3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ ተጀመረ።

62

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በካይሮ ተጀምሯል።

በድርድሩ ላይ ባልተፈቱ የቴክኒካል እና የሕግ ማእቀፍ ጉዳዮች የተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልኡካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ.ር) አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርኾዎች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሐዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርሕ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሠራም አምባሳደር ስለሺ ገልጸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሀገሪቱን ቁልፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማት ደኅንነትን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች የማስጠበቅ ሥራዎችን እየሠራን ነው” የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር
Next articleከ12ሺህ በላይ የሥራ ላይ ሠልጣኞችን ተቀብሎ እያሠለጠነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ፡፡