በአማራ ክልል የመጣውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ እዝ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች፦

38

1. እንደየ አካባቢዎቹ የሰላም ኹኔታ የተቀመጡ የሰዓት እላፊ ገደቦችን ማሻሻል። ይህም በየቀጣናዎቹ ኮማንድ ፖስቶች ይገለጻል ተብሏል።

2. የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተጠናከረ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል።

3. በየደረጃው የሚገኘው አመራር እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የሕዝብን የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እየተከታተሉ እንዲፈቱ እና

4. የክልሉ የጸጥታ ኀይሎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሥጋት ነጻ ያደረጋቸውን አካባቢዎች በፍጥነት እየተረከቡ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባቸው ወስኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክልሉ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተሳተፉ ነው” ግብርና ቢሮ
Next articleበሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የኾነ ዓለም አቀፍ የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ሽልማት በአዲስ አበባ ሊካሄድ መኾኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።