ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕፃናት እና ለወጣቶች የሚኾን የስፖርት ማዘውተሪያ አስገንብተው አበረከቱ።

90

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕፃናት እና ለወጣቶች የሚኾን የስፖርት ማዘውተሪያ አስገንብተው አበረከቱ።

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕፃናት እና ለወጣቶች የሚሆን የስፖርት ማዘውተሪያ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ አስገንብተው ዛሬ አበርክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ሁሉም በየመስኩ አድርጎ በማሳየት፣ ኾኖ በመገኘት እና በጎ አርዓያ በመኾን ኀላፊነቱን ቢወጣ ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር በመኾኗ ዛሬ የዘራነው መልካም ዘር ነገ መልካም ውጤት ያመጣል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ”ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ያስመረቅነው የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ለዚህ ማሳያ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

Previous articleየኤሲሚላን እና ጁቬንቱስ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል።
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም ዕትም