በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ።

13

ባሕር ዳር: ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

የ2023 የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ኬንያዊ አትሌት ካንዲ ኪቦውት በ57 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል፡፡

አትሌት ሀጎስ ገብረሕይወት በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ በ57 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡ አትሌት ዮሚፍ ከጄልቻ 3ኛ ደረጃን ሲይዝ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ የውድድሩን 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የሰዓት ገደብ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታወቀ።
Next articleየኤሲሚላን እና ጁቬንቱስ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል።