የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሲቀጥል የሳምንቱን ታላቅ ጨዋታ ያስተናግዳል።

12

ባሕር ዳር: ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሦስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ባሕር ዳር ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ፊልሚያ ተጠባቂ ነው።

የጣና ሞገዶቹ ቀደም ብለው ባደረጓቸው ሁለት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ አሰመዝግበዋል።በአንፃሩ ቡናማዎቹ ያደረጓቸውን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ ስኬታማ ጅማሮ ላይ ናቸው።

በዛሬው ግጥሚያ የጣና ሞገዶቹ አሸነፈው ወደ መሪዎቹ ለመጠጋት ቡናዎች ደግሞ ጥሩ አጀማመራቸውን ለማስቀጠል ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ጨዋታ ቀደሞ ቀን 9 ሰዓት አዳማ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ይጫወታሉ።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ የመጣውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ እዝ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታወቀ።
Next articleበእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና ማንችስተር ዩናይትድ ድንቅ የእግር ኳስ ታሪክ የሠሩት ሰር ቦቢ ቻርልተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡