
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በባሕር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ-ልማቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
አመራሮቹ በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለውን የአባይ ተለዋጭ ድልድይ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
የባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዲዮምም በአመራሮቹ የተጎበኘ ሲሆን በቀጣይ ስታዲየሙን ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል።
በተመሳሳይ በክልሉ ሥልጠና እየተከታተሉ ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራር አባላት በባሕር ዳርና ደሴ ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎች መጎብኘታቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!