
ቅዱስ ጊዮርጊስ በተከታታይ ለሦስተኛ ጊዜ አሸነፈ።
ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ቅዱስ ጊዮርጊስ በተከታታይ ለሦስተኛ ጊዜ አሸንፏል።
በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን ሻሸመኔ ከተማ 3 ለ 2 ረትቷል።
ለቅዱስ ጊዮርጊስ አቤል ያለው ሁለት ግቦችን እና በረከት ወልዴ አንድ ግብ አስቆጥረዋል። ያሬድ ዳዊት እና አለን ካይዋ ደግሞ ለሻሸመኔ ከተማ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ፈረሰኞቹ ያደረጓቸውን የመጀመሪያዎቹን ሦስቱንም ጨዋታዎች ድል አድርገው 9 ነጥብ መሰብሰብ ችለዋል። በአንጻሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት ሻሸመኔ ከተማዎች ያደረጓቸውን ሦስቱንም ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።
በአወል ከበደ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!