
ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2016 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ይጀመራል።
ውድድሩ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንደሚጀመር የደብረ ብርሃን ከተማ እግርኳስ ቡድን አሠልጣኝ ሰለሞን አየለ ተናግረዋል።
ቡድኑ የዝግጅት ጊዜ ማነስ እና የልምምድ መስሪያ ቦታ ማነቆ ሊኾንበት ይችላል ብለዋል አሰልጣኙ።
ያም ቢኾን በችግርም ውስጥ ውጤታማ ለመኾን ይሠራል ነው ያሉት።
ለዚህም ወቅታዊ የቡድኑ መንፈስ እና የሥነ ልቦና ደረጃ አበረታች ስለመኾኑ አመላክተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ እግርኳስ ቡድን በ1975 ዓ.ም ነበር የተመሰረተው።
በ1994 ደግሞ የአማራ ክልል ክለቦች ሻምፒዎና ሻምፒዮን መኾኑ ይታወሳል፡፡
ዘጋቢ፡- ዮናስ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!