
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል።
በዚህ የኢትዮጵያ፣ የእስራኤል እና የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችል ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገውም መክረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!