
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በግብርና ዘርፍ ትብብርን ማስፋት ብሎም ኢንዱስትሪን ማእከል ያደረገ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) የዕለቱ ውሎ ሁለተኛ መርሐ-ግብር በ3ኛው ቢአርአይ ከፍተኛ ጉባዔ ላይ “Connectivity in an Open Global Economy” በሚል ጭብጥ ንግግር ማቅረብ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው በኢትዮጵያ የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭን ስኬታማ ልምድ አጋርተዋል::
በግብርና ዘርፍ ትብብርን ማስፋት ብሎም ኢንዱስትሪን ማእከል ያደረገ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባም ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!