
አዲስ አበባ: ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የደረጃዎች ቀን በየዓመቱ ጥቅምት 4 ይካሄዳል። የዚህ አካል የኾነ በጥራት ላይ የሚመክር የተለያዩ ተቋማት ሥራ ኀላፊዎች መድረክ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ (ዶ.ር) እንዳሉት ደረጃ የማይሄድበት እና የማይገባበት የሌለ ከመኾኑ ጋር ተያይዞ የኑሮ መሠረት ነው። ሁሉም ደረጃዎችን በመተግበር ለጥራት ስኬት መሥራት አለበትም ብለዋል። የኑሯችን መሰረት የኾነውን የደረጃዎች ጥራት በመተግበር ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ዶክተር መሰረት።
የኢትዮጵያ ነዳጅ እና ኢነርጅ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሁሪያ አሊ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የምግብ ነክ እና እና የመድኃኒት ነክ ምርቶች ጥራት እና ደረጃዎችን ያልጠበቁ ናቸው በሚል አንዳይገቡ ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ “ላቦራቶሪዎችን በማብዛት እና የጥራት አቅምን በማሳደግ አብረን እንሠራለንም” ብለዋል።
ደረጃዎች የሁሉም ሥራ አካል በመኾናቸው ደረጃዎችን ማስጠበቅ የሁሉም አካል ኀላፊነት እንደኾነም አስገንዝበዋል። የደረጃዎች ግብ የሕይወትን መሰናክል ማስወገድና ኑሮን ምቹ ማድረግ ነው ተብሏል።
የደረጃዎች ሚና ዓለም አቀፍ ለዘላቂ ልማት ግብ መሳካት በሚል ጽሑፍ ቀርቦ ወይይት እየተደረገበት ነው። የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት እና የግል ድርጅት ኀላፊዎች በፎረሙ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!