“በባለብዙ ወገን መድረኮች አካታችነትን ማረጋገጥ ተገቢ ነዉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

39

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ንግግር አድርገዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንግግራቸው የቻይና-አፍሪካን ግንኙነት ጥንተ መሰረት እና እድገት አውስተው በቢአርአይ የመሰረተ ልማት ክንውን በአፍሪካ አህጉር የተጣለውን ጠንካራ የትብብር መሰረት አንስተዋል።

በማደግ ላይ ያለውን የአፍሪካን ተፅእኖ የመፍጠር አቅም አፅንዖት በመስጠትም በባለብዙ ወገን መድረኮች አካታችነትን ማረጋገጥ ተገቢ እንደኾነ ማስረዳታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበከተማዋ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር እየሠራ መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከብሪክስ ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍ ጋር ተወያዩ።