
ባሕር ዳር: ጥቅምት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ከምድብ ሦስት ማልታ ከዩክሬን፣ ከምድብ ሰባት ሊቱኒያ ከሀንጋሪ፣ ሰርቢያ ከሞንቴኔግሮ ፣ከምድብ ስምንት ፊንላንድ ከካዛኪስታን ይጫወታሉ።
በተለይ በምድብ ሦስት የተደለደሉት እንግሊዝ እና ጣልያን ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ላይ 90ሺህ ተመልካች በሚይዘው በለንደኑ የዌምብሌይ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ በእጅጉ አጓጓጊ ኾኗል።
ምድቡን እንግሊዝ አምስት ጨዋታዎች አድርጋ በ13 ነጥብ እየመራችው ትገኛለች። ጣልያንም በአምስት ጨዋታዎች 10 ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በየምድባቸው ስድስት ጨዋታዎችን ያደረጉት ዩክሬናውያን በ10 ነጥብ ፣ ሜቄዶኒያ በሰባት ነጥብ እንዲሁም ማልታ ያለምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ በቂያችን ቢኾንም የምንጫወተው ግን ለማሻነፍ ነው ፤ ካለን ስብስብና የተጫዋቾች አሁናዊ ተነሳሽነት አኳያም እናሸንፋለን ብለዋል።
የጣልያኑ አለቃ ሉቺያኖ ስፖሌቲ በበኩላቸው በእስካሁን የብሔራዊ ቡድኑ ታሪክ እንግሊዝን 13 ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ነን ብለዋል። ምንም እንኳ በመጀመሪያው ግንኙነታችን በራሳችን ስህተት በሜዳችን ብንረታም ከስህተታችን ተምረንና ተጠናክረን ወደ ሜዳ በመግባት ለማሸነፍ እንጫወታለን በማለት ተናግረዋል።
ለጀርመኑ የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ካለፉት ሀገራት መካከል አዘጋጇ ጀርመን ፣ ከምድብ አንድ ስፔንና ስኮትላንድ ፣ከምድብ አራት ተርኪዬ ፣ከምድብ ስድስት ቤልጀየም እና ኦስትሪያ ፣ከምድብ ሰባት ፈረንሳይ እንዲሁም ከምድብ 10 ፖርቱጋል ይገኙበታል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!