“በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ወጤት አስመዝግበዋል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

73

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኅላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የክልሉን ውጤት ትንተና አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ነው።

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አማራ ክልል በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥም ኾኖ በአንጻራዊነት ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ተብሏል።

ክልሉ ከአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ እና ሀረር በመቀጠል አራተኛ ደረጃ ላይ የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ፤ በችግሮች ውስጥ ኾነን የተገኘው ውጤት በትጋት ከሠራን አበረታች ውጤት ይገኛል ብለዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 በላይ እና በማኅበራዊ ሳይንስ ከ500 በላይ ከፍተኛ ውጤት ነው ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ “በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ወጤት አስመዝግበዋል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን በማበረታታት ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ይገባል” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next article“8 ሺህ 434 ተማሪዎች 50 በመቶ እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል” ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ