
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመኾን በቻይና ታላቁ የሕዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል::
በሁለትዮሽ ውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ሺ በኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል::
የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ኹኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል::
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመኾኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ኾኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖት አንስተዋል። በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች-በግብርና ማኑፋክቸሪንግ አይሲቲ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል:: መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!