ምክር ቤቱ 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

24

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ በጉባዔው፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በደቡብ ኮሪያ እንዲሁም በህንድ ሪፐብሊክ መንግሥታት መካከል የዲፕሎማቲክ እና ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ የሚያፀድቅ ይኾናል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያና በሊባኖስ መንግሥታት መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ይመራል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት መካከል በሁለትዮሽ ወታደራዊ ቴክኒካዊ ትብብር ወቅት የተገኙ የአዕምሯዊ የፈጠራ ሥራ ውጤቶች እና ንብረቶች የጋራ ጥበቃ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉት ምክክር ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ያላትን ፍላጎት ያሳየ ነው” ቢልለኔ ስዩም
Next articleየኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ኹኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ተገለጸ።