የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ለሀገር በመሥራት ሊኾን እንደሚገባ ተገለጸ።

20

ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለኢትዮጵያዊያን የነጻነትና የሀገር ፍቅር መገለጫ መኾኑን የሚናገሩት የደብረ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካዊያን የነጻነት ምሳሌ መኾኑንም ያነሳሉ።

የታሪክ መምህሩ ግርማ አበበ የኢትዮጵያ ትንሳዔ እውን እንዲኾን ኢትዮጵያዊያን ከባድ መስዋትነት መቀበላቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ወራሪዎች በተደጋጋሚ ወረራ ለማድረግ በሞከሩበት ወቅት ሰንደቃቸውን በማስቀደም ለሀገራቸው ሉዓላዊነት መከበር ባደረጉት ተጋድሎ ለሌሎች አፍሪካዊያን ሀገራትም ተምሳሌት መኾናቸውንም አስረድተዋል።
የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር መምህሩ ዳንኤል ጌታቸው

ባርነትን የማይቀበሉ፣ ፍትሕን አብዝተው የሚሹ እና ነጻነታቸውን በእጅጉ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ያደረጉት ተጋድሎ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ብርሃን ፈንጣቂ ነው ብለዋል። መምህሩ የአፍሪካዊያን ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያ መወሰዱ አንዱ ማሳያ መኾኑንም አንስተዋል።

በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ፍቅር ስሜታቸው የሀገራቸውን ገናና ታሪክ በመክተባቸው ለመላው አፍሪካዊ ተምሳሌት መኾናቸውንም ተናግረዋል።

መምህራኑ “የአሁኑ ትውልድ ወቅቱ የሚጠይቀውን ተጋድሎ በማድረግ የሀገራቸውን የስኬት ታሪክ ሊጽፉ ይገባል” ብለዋል

ዘጋቢ፦ ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰንደቅ ዓላማችን የማንነታችን መገለጫ ብቻም ሳይኾን የከፍታችን ምልክትም ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ ተማሪዎችና መምህራን
Next article“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉት ምክክር ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ያላትን ፍላጎት ያሳየ ነው” ቢልለኔ ስዩም