“ሰንደቅ ዓላማችን የማንነታችን መገለጫ ብቻም ሳይኾን የከፍታችን ምልክትም ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ ተማሪዎችና መምህራን

26

ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ሰንደቅ ዓላማችን ልናከብር ይገባል ብለዋል አሰተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የደብረ ብርሃን ከተማ ተማሪዎችና መምህራን።

ያለ ሰንደቅ ዓላማ ሀገር ሙሉ እንደማትኾን የሚናገሩት መምህር ሙላቱ ፈለቀ ይህንን ቀድመው የተረዱ ቀደምት አባቶች ለሰንደቅ ዓላማቸው ሲሉ ክቡር ሕይወታቸውን ሰጥተዋል ብለዋል።

ሰንደቅ ዓላማችን የማንነታችን መገለጫ ብቻም ሳይኾን የከፍታችን ምልክትም ነው” ያሉት ተማሪዎቹ ይህንን ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን የማንነት መለያ ማክበርና ማስከበር ደግሞ የዛሬው ትውልድ ኀላፊነት እንደኾነም ገልጸዋል።

“በአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን ሰንደቅ ዓላማቸውን ከፍ አርገው ሲያውለበልቡ ስናይ የደስታ እንባ ነው የሚተናነቀን ይህም ለሰንደቅ ሲባል የተከፈለውን ዋጋ ስለምናስታውስ ነው” ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።

ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሕዝቡ ሚና የጎላ ነው ተባለ።
Next articleየሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ለሀገር በመሥራት ሊኾን እንደሚገባ ተገለጸ።