
ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጰያ በጣሊያን ሮም ዛሬ በተጀመረው የዓለም ምግብ ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው።
በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በአረንጓዴ ልማት፣ በመስኖ ስንዴ ልማት ምርትና ምርታማነት እና በሌማት ትሩፋት የተከናወኑ ተግባራትንና ተሞክሮዎችን የኢትዮጵያ ልዑክ በመድረኩ ላይ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ልዑኩ ከመድረኩ ጎን ለጎንም ከተለያዩ የዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ አሕጉር እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እና መልኅቅ ድርጅቶች ጋር አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፎረሙ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!