“የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ለሰላም መስራት ይገባል” የእብናት ከተማ ነዋሪዎች

22

ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በእብናት ከተማ የመብራት ኃይል ማስፋፊያ ሥራ በጸጥታ ችግር ምክንያት ማቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል ባለስልጣን የእብናት አገልግሎት መስጫ ማዕከል አስታወቀ፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ከተማ አዲስ የተገነቡ ቤቶችን የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የመስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

ማዕከሉ አገልግሎቱን 1 ሺህ ቤቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የምሰሶ ተከላ፣ የገመድ ዝርጋታ እና የቆጣሪ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ቀሪው ሥራ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ባለመብቃቱ ነዋሪዎች መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

ዋና ሳጅን አብራራው ሽፈራው ቤት ገንብተው መብራት እንዲገባላቸው ከሚጠባበቁት መካከል ናቸው፡፡ መብራቱ ተጠናቅቆ አገልግሎት ባለመሥጠቱ ለአላስፈላጊ ወጭ መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ለመብራቱ ሥራ መጓተት በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደኾነም ዋና ሳጅን ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ቄስ ዓባይ ዓለሙ ናቸው፡፡ ቄስ ዓለሙ በእብናት ከተማ ቤት ሠርተው መብራት እንዲገባላቸው ከሚጠባበቁት መካከል አንዱ ናቸው፡፡

የመብራት ዝርጋታው በሚጠናቀቅበት ወቅት የጸጥታ ችግር ማጋጠሙ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

ሠላም ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ቅድሚያ ሰላም ያስፈልጋል ስለሆነም ለሰላም እንዲሰፍን ርብርብ እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

ሰላም ለሁሉም ነገር ወሳኝ መኾኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ከተማቸው ሰላም እንዲኾንና የተጀመሩ ልማቶች እንዲጠናቀቁ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ዲስትሪክት የእብናት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ሃብታሙ ይግለጥ በከተማው በአዲስ ለተገነቡ 1 ሺህ ቤቶችን የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ የምሰሶ ተከላና ገመድ ዝርጋታ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስም ቀሪው ሥራ ተጠናቆ ነዋሪዎችን የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ቢታሰብም በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሥራው መቋረጡን ገልጸዋል፡፡

ሰላም ለሁሉም ነገር ወሳኝ መኾኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ከተማቸው ሰላም እንዲኾንና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ለሰላም መስራት ይገባል ብለዋል፡፡የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ለሰላም መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ “የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ለሰላም መስራት ይገባል” ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሉዓላዊነትና የነፃነታችን ዓርማ የኾነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን” ኮሚሸነር ደመላሽ ገብረሚካኤል
Next articleየፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ያለው እንዲኾን ጥረት እየተደረገ መኾኑን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለጸ፡፡