
ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያ ኢኳቶርያል ጊኒን 4ለ1 በኾነ ውጤት ረትታለች፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ነው ኢትዮጵያ የኢኳቶርያል ጊኒ አቻውን 4 ለ1 ማሸነፍ የቻለው፡፡
ንግሥት በቀለ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር መሳይ ተመሥገን እና እሙሽ ዳንኤል አንድ አንድ ግብ ለኢትዮጵያ ማስቆጠር ችለዋል።
በድምር ውጤት ኢትዮጵያ ኢኳቶሪያል ጊኒን 5 ለ 2 ነዉ ያሸነፈችው።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር ከማሊ እና አልጄርያ አሸናፊ ጋር የምትጫወት ይኾናል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!