የጣና ሞገዶቹ መድንን አሸነፉ።

22

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና ሞገዶቹ መድንን በማሸነፍ ድል ቀንቷቸዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የአራተኛ ቀን ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ የተገናኙት ባሕር ዳር ከተማ እና መቻል በባሕር ዳር 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በ12ኛው ደቂቃ ፍሬው ሰለሞን ለጣና ሞገዶቹ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል። ሁለተኛውን ግብ ደግሞ ሀብታሙ ታደሰ ኳስን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሽመልስ በቀለ በ71ኛው ደቂቃ የመቻልን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

የጣና ሞገዶቹ በሁለት ጨዋታ አንዱን አሸንፈው በአንዱ ተሸንፈው ሦስት ነጥብ መሰብሰብ ችለዋል። መቻልም በመጀመሪያው ሳምንት የሊጉን ጨዋታ አሸንፎና ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ተሸንፎ ሦስት ነጥብ አለው።

በሊጉ መርሐ ግብር መሰረት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ሻሸመኔ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

በአወል ከበደ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአትሌት መሠረት በለጠ የአምስተርዳም ማራቶንን አሸነፈች።
Next articleኢትዮጵያ ኢኳቶርያል ጊኒን 4 ለ1 አሸነፈች።