አትሌት መሠረት በለጠ የአምስተርዳም ማራቶንን አሸነፈች።

23

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር መሠረት በለጠ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ 21ሴኮንድ በኾነ ሰዓት አሸንፋለች።

መሠረት ያሸነፈችው የግሏን ምርጥ ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል ነው። በጥር ወር በዶሃ 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 46 ሴኮንድ ካጠናቀቀችበት ድሏ በኋላ ይህ የዓመቱ ሁለተኛ ድሏ መኾኑን ከዓለም አትሌትክስ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

መሠረት አብዛኛወን ርቀት ወጥ በኾነ ፍጥነት የሮጠች ሲሆን፣ የሀገሯ ልጆች መሠረት አበባየሁ እና አሸቴ በክሪ እንዲሁም ኬንያዊቷ ዶርካስ ቱቶይክ ተፎካካሪዎቿ ነበሩ።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ መሠረት አበባየሁ እና አሸቴ በክሪ 2ኛ እና 4ኛ ሲወጡ ኬኒያዊቷ ዶርካስ ቱተይክ 3ኛ ኾና ማጠናቀቋንም መረጃው ያመለከታል፡፡

በተመሳሳይ ቦታ በተደረገው የወንዶች ውድድር ኬንያውያኑ ጆሹዋ ቤሌት፣ ሲብሪያን ኮቱት እና ቤትዌል ቹምባ ተከታትለው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ወጥተዋል። ኢትዮጵያውያኑ ብርሃኑ ለገሰ፣ ለሚ ብርሃኑ፣ ባዘዘው አስማረ፣ ሙሉገታ ደባሱ እና ሃይማኖት ዓለሙ ከ4ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደሴ ማዕከል ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ መሪዎች በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ ተቋማትን ጎበኙ።
Next articleየጣና ሞገዶቹ መድንን አሸነፉ።