
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ደሴ ማዕከል ስልጠና ላይ የሚገኙ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ መሪዎች በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ ተቋማትን ጎብኝተዋል።
በቅርቡ የተገነባውን ዘመናዊ የመናኸሪያ ማእከልና የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክን የመስክ ጉብኝትና ምልከታ አድርገዋል።
በብልጽግና ፓርቲ አዘጋጅነት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ላይ በአማራ ክልል ደሴ ማዕከል ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በኮምቦልቻ ከተማ በቅርቡ የተገነባውን ዘመናዊ የመናኸሪያ ማእከልና የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክን የመስክ ጉብኝትና ምልከታ አድርገዋል።
በአማራ ክልል በሁለንተናዊ ለውጥ እና የእድገት ጉዞ ላይ ስለመኾናቸው ማሳያ ሊሆኑ ከሚችሉት ከተሞች መካከል የፍቅርና የመቻቻል ከተማዋ ኮምቦልቻ ቀዳሚዋ ስትኾን የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ተጎብኝተዋል።
እንደ ብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ መሪዎቹ በጉብኝቱ መልካም ልምድ የሚቀስሙበትና እንደሀገር የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳለጥ የሚያስችል አቅምና ልምድ ያገኙበት መኾኑ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!