አትሌት አልማዝ አያና በህንድ የግማሽ ማራቶን ሩጫን አሸነፈች።

33

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በህንድ በተካሄደው የዲልሂ ግማሽ ማራቶን ሩጫ አትሌት አልማዝ አያና አሸንፋለች።

አትሌት አልማዝ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ 7 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ፈጅቶባታል።

አትሌቷ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኃላ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተመልሳ ያስመዘገበችው ውጤት ነው። በዉድድሩ የኡጋንዳ እና የኬንያ አትሌቶች 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል።

በተመሳሳይ በወንዶች በተካሄደ ሩጫ ኬንያዊው አትሌት ዳንኤል ኤቢንዮ በ59 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ 1ኛ በመውጣት አሸንፏል።

ሌለው ኬንያዊ አትሌት ቻርለስ ማታታ 2ኛ ደረጃን ሲያገኝ ኢትዮጵያዊው አትሌት አዲሱ ጎበና 3 ደረጃን ይዞ መፈጸሙን ኤኤምኤን ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጎንደር – የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት 12 በሮችን ይጎብኙ
Next article“የመጣሁት ወደ ሁለተኛዋ ቤቴ ነው” ፋጡማ ሙሳ ከአፋር