
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብዙ ጊዜ የአጼ ፋሲል ግቢ በመባል የሚታወቀው ቦታ ስፋት 70 ሺህ ካሬ ሜትር ይሆናል፡፡ ግቢው ከ17ኛው እና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ከነበሩት መካከል የስድስቱን አብያተ መንግሥታትና ሌሎች በርካታ የሕንፃ ፍርስራሾችን ይዞ ይገኛል፡፡
የአፄ ፋሲል ግቢ ቀደም ብሎ አገልግሎት የሚሰጡ አሥራ ሁለት በሮች ነበሩት፡፡
ከፊት በር ጀምሮ በስተቀኝ የሚገኙት ጥንታዊ በሮች የራሳቸው ልዩ መጠሪያ አላቸው፦
1. ፊት በር (ጃን ተከል በር)
2. ወንበር በር
3. ራስ በር
4. አዛዥ ጠቋሬ በር
5. አደናግር በር
6. ኳሊ በር
7. እምቢልታ በር
8. ባልደራስ በር
9. እርግብ በር
10. ቀጭን አሸዋ በር
11. እንኮይ በር
12. እቃ ግምጃ ቤት በር
ምንጭ፦ የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ
ወደ ታሪካዊቷ የነገስታት ባለአሻራ ውቧ ጎንደር ከተማ ጎራ ሲሉ በዩኔስኮ የተመዘገበውን የፋሲል ቤተ መንግሥትን ጨምሮ ሌሎችን በከተማዋ እና በዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ መሥህቦች ይጎበኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!