“የአማራ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይና ሰው ወዳድ ነው” የብልጽግና ፓርቲ ሰልጣኞች

49

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች በባሕርዳር ሥልጠና እየወሰዱ ነው፡፡

በሥልጠናው የተገኙ መሪዎች የከተማዋን የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

የፓርቲው ሠልጣኞች የአማራ ሕዝብ ሰላም ወዳድ ሕዝብ መኾኑን በተደጋጋሚ ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል፡፡ ሰልጣኞቹ ከመምጣታቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ ኹኔታ ስጋት እንደነበራቸውም አስታውሰዋል፡፡ በክልሉ ዋና ከተማ ያለው እውነታና ሕዝቡ ለሰላም የሚሰጠው ዋጋ ከፍ ያለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የመጡት ቱባ ማማ ከመምጣታቸው አስቀድሞ የሰሙት የሰላም ወሬና መሬት ላይ ያለው ሰላም የተራራቀ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በሚዲያ የሰሙት እና በተግባር ያዩት እንደማይገናኝም ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ሰላም መሰፍኑን እና የልማት እቅስቃሴዋ ጥሩ ላይ መኾኑን ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል፡፡ ወደ አማራ ክልል በመምጣታቸው እና ከሰላም ወዳድ ሕዝብ ጋር በመገናኘታቸው ደስተኛ መኾናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ባሕርዳር የፍቅር ከተማ ናት የሚባለውን በተግባር ያዩበት፣ የሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነትን የተመለከቱበት እና ሰላማዊ መኾኑን ያረጋገጡበት መኾኑን አንስተዋል፡፡ በየአካባቢው ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ማሳደግ እና ሀገርን ወደ ተሻለ ልማት ማሸጋገር እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ከአፋር ክልል የመጡት ነስራ ዑዳ ስለ አማራ ክልል የሚወራውና በውስጡ ያለው አኹናዊ ኹኔታ የተለያዬ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በባሕርዳር የሚያደርጉት ቆይታ እንደቤታቸው እየተሰማቸው እንደኾነም ተናግረዋል፡፡ የሕዝቡ ፍቅር እና እንክብካቤ አስደናቂ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ እንደ ሀገር የጋራ በሚያደርገን ኢትዮያዊነት ላይ ትኩረት እናድርግም ብለዋል፡፡

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጡት ባርክደርድም አሕመድ ከሚወራው አኳያ ወደ አማራ ክልል ሲመጡ ስጋት እንደነበረባቸው ተናግረዋል፡፡ ወደ ክልሉ ከመጡ በኋላ ለየት ያለ አቀባበል እንደጠበቃቸውም ገልጸዋል፡፡ ሕዝቡ ለሰላም እንደሚቆም ያየንበት ነው ብለዋል፡፡ የተደረገላቸው አቀባባል እና እንክብካቤ የሚያስመሰግን እንደኾነም ተናግረዋል፡፡

ወደ አማራ ክልል ስንመደብ እንዴት የሚል የስጋት ጥያቄ ጠይቀን ነበር ነው ያሉት፡፡ መጥተው ሲያዩት ግን ለስጋት የማያበቃ እና በሰላማዊ መንገድ ሥልጠናቸውን እንዲወስዱ የሚያስችል ሰላም እንዳለ አረጋግጠዋል።

በክልሉ አሁን ላይ ያለውን ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ችግሮችን በንግግርና በውይይት መፍታት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ ግጭት ሰውን እና ንብረትን እንደሚያሳጣም ገልጸዋል፡፡ መንግሥትም የማኅበረሰቡን ችግር በመለየት መፍታት አለበት ነው ያሉት፡፡

ከሶማሌ ክልል የመጡት ሙሐሙድ መሐመድ የአማራ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይና ሰው ወዳድ ሕዝብ ነው ብለዋል፡፡ ከመምጣታቸው አስቀድሞ ስለ ባሕርዳር ከተማ ሲወራ የነበረው እና ያገኙት እውነት የማይገናኝ መኾኑን አንስተዋል፡፡ ሰላም በሌለበት የሚታሰብ ነገር አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡ በአንደኛው አካባቢ ያለው የሰላም እጦት ሌላውንም ይነካል ያሉት ሙሐሙድ ሰላምን በሁሉም ቦታ ማስፈን ይገባል ነው ያሉት፡፡ የባሕርዳር ሕዝብ ላደረገላቸው አቀባባል እና ለሰጣቸው ፍቅርም አመሰግንዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአማራ ክልል ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደሚወራው አይደለም” የብልጽግና ፓርቲ ሰልጣኞች
Next article“እኛ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያን በወጉ የተረዳናት አይመስለኝም” ጣሰው ከበደ ከደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ