የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አካል የኾኑ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

55

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱን ቀጥሏል።

በመጀመሪያው ሳምንት በኢትዮጵያ መድን 3 ለ 2 የተረታው የጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 3 ለ 2 ከረትታው መቻል ጋር ቀን 9 ሰዓት ይጫወታል።

ሻሸመኔ ከተማ ደግሞ ሀዋሳ ከተማን ምሽት 12 ሰዓት ላይ ያስተናግዳል።

ባሕር ዳር ከነማ ከመቻል ጋር ዛሬ በሚያካሂደው ጨዋታው ከኢትዮጵያ መድን ጋር ሲጫወት የታየበትን የተከላካይ መስመር ክፍተት አርሞ ወደ ሜዳ መግባት ይጠበቅበታል።

የጣናው ሞገድ በመጀመሪያው ሳምንት የአጥቂው ክፍል ያሳየውን ተናቦ የመጫወት ጥንካሬ በዛሬው ጨዋታ ይበልጥ አጠናክሮ ከቀጠለ መቻልን ሊያሸንፈው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

መቻል በበኩሉ የአጥቂዎች ብስለትና የመናበብ ጥምረት በባሕር ዳር ተከላካዮች በአንድ ለአንድ ያጨዋወት ሥልት ካልተገታ ባሕር ዳር ከነማን የማሸነፍ እድል አለው።

ሀዋሳ ከተማም በመጀመሪያው ሳምንት ከፋሲል ከነማ ጋር 3 ለ 3 በተለያየበት ጨዋታ የነበረበትን የመከላከል ክፍተትና መዘናጋት በማረም በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ሲያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ በዛሬው ጨዋታም ይበልጥ አጠናክሮ ወደ ሜዳ መግባት አሸናፊ ያደርገዋል። ይሁንና የሻሸመኔ ከተማ ጠንካራ የተከላካይ መስመር በቀላሉ በሀዋሳ ከተማ አጥቂዎች የሚረታ አይመስልም።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባሕር ዳር በልማት ጎዳና ላይ የምትገኝ ጽዱ ከተማ ናት” የብልጽግና ፓርቲ ሠልጣኞች
Next articleሉሲዎቹ ከኢኳቶርያል ጊኒ አቻቸው ጋር ይጫወታሉ።