ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

116

ባሕር ዳር: ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የምሥራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌትናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ፣ የፍኖተሰላም ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል መለስ መንግሥቴን ጨምሮ ከፍተኛ የምንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት ፍኖተ ሰላም ከተማን ጨምሮ አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የሰላም ችግር ገጥሟቸው ቆይቷል። ከሰሞኑም ፍኖተሰላም ከተማ ወደ አንፃራዊ ሰላም ተመልሳለች። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተጀመረው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ነው ከነዋሪዎች ጋር የተወያዩት። በተከሰተው ግጭትም አካባቢው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እንደደረሰበት በውይይቱ ተነስቷል።

ርእሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ክልሉ በሰሜኑ ጦርነት ከደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ሳያገግም ወደ ሌላ ውድመት መሄድ የክልሉን ሕዝብ የባሰ ጉዳት ላይ የሚጥል መሆኑን ነው የተናገሩት። ክልሉ በልማት፣ በመልካም አሰተዳደር እና በሰላም ተጠቃሚ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል። ተወዳዳሪ ክልል ለመፍጠር ስለለሰላም መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“7 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች አስቸካይ የምግብ እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleጊዜያቸው ያለፈባቸው እና በአግባቡ ያልተቀመጡ መድኃኒቶች፣ ምግብ እና ምግብነክ ነገሮችን ላለመጠቀም ጥንቃቄ እንዲደረግ ጤና ቢሮ አሳሰበ፡፡