የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ በመስከረም ወር ምርጥ ተጫዋች እና አሠልጣኝ ይፋ ኾነ።

48

ባሕር ዳር: ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ የመስከረም ወር ምርጦች ሲታወቁ የቶትንሃሙ አሠልጣኝ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አሸናፊ ኾነዋል። የቶትንሃም አምበል ሰን ሁንግ ሚን የወሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሏል።

ሰን በመስከረም ወር በቶትንሃም ባደረጋቸው አራት የፕሪሜር ሊግ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።አሁን ቶትንሃም በፕሪሜር ሊጉ አናት ላይ ለመቀመጡም ትልቅ ድርሻ ነበረው።

በተመሳሳይ በአሠልጣኞች ዘርፍ የሚሰጠውን የወሩ ምርጥነት የቶትንሃሙ ኤንጀ ፖስቴኮግሉ አሸንፏል። አሠልጣኙ የነሐሴ ወርም ምርጥ አሠልጣኝ ተብሎ ተመርጦ ነበር። ጀምስ ማዲሰን ደግሞ በተጫዋቾች ዘርፍ አሸናፊ የነበረ ሲኾን የቶትንሃም አሠልጣኝ እና ተጫዋች የወሩ ምርጥ ተብለው ሲመረጡ በከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ መኾኑ ነው።ይሄ በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያ መኾኑን ደይሊ ሜይል ዘግቧል።

የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ በ2019/20 የውድድር ዘመን መጀመሪያ ሁለት ተከታታይ የፕሪሜር ሊግ ወራት ኮከብ አሠልጣኝ መባላቸው የሚታወስ ሲኾን በዓመቱ መጨረሻ ክለባቸው የዋንጫ ባለቤት ኾኖ ነበር።

ዘጋቢ:- አስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ በጠንካራ ፉክክር ማራኪ የእግር ኳስ ጨዋታ የሚታይበት ይኾናል” የምንጊዜም የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች
Next articleኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ሚስኵርም 30/2016 ዓ.ስ