“ለሀገር መታመን ኩራትም ስኬትም ነው” ታማኝ ግብር ከፋዮች

57

ባሕር ዳር: ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ተቋማትና ግለሰቦች ግብርን በታማኝነት በመክፈል፣ ሀገርን በጋራ እናልማ ሲሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች ጥሪ አቅርበዋል። በአምስተኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር በፕላቲኒየም፣ በወርቅ እና ብር ደረጃ የተለዩ ግብር ከፋዮች ተሻላሚ ኾነዋል።

ግብር ከፋዮቹ እንደሚናገሩት ለሀገር ታማኝ ኾነን ለዕውቅናና ሽልማት በመብቃታችን ኩራት እና ደስታ ተሰምቶናል፤ ለቀጣይ ሥራችንም ትልቅ ስንቅ ነው ብለዋል።

ለሀገርና ሕዝብ አስፈላጊ የኾኑ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚገኙት ከግብር በሚገኝ ገቢ በመኾኑ ታማኝ በመኾን መክፈል አለብንም ብለዋል። ይህን በማድረጋችን ዕውቅና አግኝተናል ለሀገር ልማትም አስተዋጽኦ እንዳበረከትን ይሰማናል ነው ያሉት። “ለሀገር መታመን ኩራትም ስኬትም ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

መንግሥት ሀገር ይመራል ፤ አቅጣጫ ይሰጣል እኛ ደግሞ ግብር በመክፈል ሀገርን በጋራ ማልማት አለብን የሚሉት ታማኝ ግብር ከፋዮቹ ሌሎች ተቋማትም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉና በሀገራቸው እንዲመሠገኑ መልእክት አስተላልፈዋል።

ተቋማት ግብርን በአግባቡ በመክፈል ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ፣ መንግሥትም የተገኘውን ገቢ በአግባቡና በፍትሐዊነት ልማት ላይ እንዲያውል ጥሪ ቀርቧል።

ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተጠባቂው የስፔን እና የስኮትላንድ ጨዋታ በስፔን አሸናፊነት ተቋጭቷል።
Next article“በተከታታይ የተመዘገበው ጥሩ ውጤት ለእኛም መነሳሳት ፈጥሯል” የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች