
ባሕር ዳር: ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሊጉ 2ኛ ሳምንት መርኃ ግብር አካል የኾኑ ጨዋታዎች በዕለተ አርብ፣ ቅዳሜና እሑድ ይደረጋሉ።
አርብ ቀን 9፡00 ሀምበሪቾ ዱራሚ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፤ 12:00 ደግሞ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ።
በመጀመሪያው ሳምንት መርኃ ግብር ሀምበሪቾ ዱራሚ በድሬዳዋ ከተማ 2ለ1 ተሸንፏል።በአንጻሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን 4ለ1 ረትቷል።
ፋሲል ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር 3ለ3 ሲለያይ፣መድሕኖች በበኩላቸው የጣና ሞገዶችን 3 ለ 2 መርታታቸው ይታወሳል።
የፊታችን ቅዳሜም በመጀመሪያው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ የተረታው ወልቂጤ ከተማ በኢትዮጵያ ቡና ከተሸነፈው ሲዳማ ቡና ጋር 9፡00 ይጫወታል ።
ሻሸመኔ ከተማን 1ለ0 የረታው ወላይታ ድቻ አዳማ ከተማን ምሸት 12:00 ያስተናግዳል ።
በዕለተ እሑድ ደግሞ በመጀመሪያው ሳምንት በኢትዮጵያ መድን የተረታው ባሕር ዳር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 3ለ2 ከረታው መቻል ጋር ቀን 9:00 ይጫወታል ።ሻሸመኔ ከተማ ሀዋሳ ከተማን ምሸት 12: 00 ያስተናግዳል። የሁለተኛ ሳምንት የፕሪሜር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ሽፋን እንደማያገኙ መገለጹ ይታወሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!