የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ አጀንዳዎችን ላይ ተወያይቶ አጸደቀ።

48

አዲስ አበባ: ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 28/2016 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተደረገው ንግግር ላይ የቀረበለትን ሞሽን አዳምጧል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ አጀንዳዎችን ተመልክቶ በርካታ ረቂቅ አዋጆችንም አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በዕለቱ የተመለከታቸው አጀንዳዎች

👉 ፕሬዝዳንቷ በንግግር የቀረበለትን ሞሽን ማዳመጥ፣

👉 ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር አዋጅ መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴው መምራት

👉 በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኤሌክትሪክ ፕሮግራም ትግበራ የተደረገውን የ250 ሚሊዮን ብር ብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማፅደቅ

👉 ከዓለምአቀፉ የልማት ማኅበር ለሰው ሀብት ልማት ለማዋል የተገኘውን የ37 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ማፅደቅ

👉 ከጣልያን መንግሥት ለቡና እሴት ሰንሰለት ማሻሻያ የተገኘውን የ10 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ማፅደቅ

👉 ከጣልያን መንግሥት ለውኃና ኢነርጂ ዘርፍ ለተቀናጀ የውኃ ሀብት የተገኘውን የ24 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ማፅደቅ እለታዊ አጀንዳዎቹ ነበሩ። የድጋፍ ሞሽኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ውይይት ተደርጎበት የሚጸድቅ መኾኑ ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው እባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአሚኮ ወደ አዲስ ምእራፍ!
Next article