ሩኒ የበርሚንግሃም ሲቲ አሠልጠኝ ኾኖ ተሾመ፡፡

39

ባሕር ዳር: መስከረም 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ፣ የማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ክለቦች ፊት አውራሪ የነበረው ዋይኒ ሩኒ የበርሚንግሃም ሲቲ አሠልጠኝ ኾኖ ተሹሟል፡፡

ሩኒ የአሜሪካውን ዲሲ ዩናይትድን ክለብ ወደኋላ ትቶ ወደ እናት ሀገሩ እንግሊዝ ተመልሷል፡፡

አንድ ሜትር ከ76 ሴንቲ ሜትር ቁመት ያለው እና በእንግሊዝ-ሊቨርፑል ከተማ የተወለደው ሩኒ በእንግሊዛውያን ዘንድ ስመ ጥር የኾነ ተጫዋች ነው፡፡

ሩኒ ከሰማያዊዎቹ ጋር የሦስት ዓመት ተኩል ውል መፈራረሙን ቢቢሲ በዘገባው አትቷል፡፡

ሩኒን በርሚንግሃም ሲቲ አሠልጣኝ አድርጎ እንደሾመው ቢቢሲ “ምን ተሰማህ?” ሲል ጠይቆት ነበር፡፡

ሩኒም:- “የበርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ ክለብን ለማሠልጠን እድሉን በማግኜቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ፤ ቡድኑ እንዲጫወት የምፈልግበት ግልፅ ፍኖት ስላለኝም በእኔ እየተመራ የጥሩ ውጤት ባለቤት እንዲኾን በቁርጠኝነት እሠራለሁ “ ብሏል
ሩኒ የእግር ኳስ የአሠልጣኝነት ሕይወቱን የጀመረው እ.ኤ.አ በ2021 በደርቢ ካውንቲ ክለብ ነበር ፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሀገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሀሳብ 4ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ሊከበር ነው።
Next article“ማለፍ ብቻ የሚታወቅበት ትምህርት ቤት!”