
ባሕር ዳር: መስከረም 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።
የሁለተኛ ሳምንት ውድድርም ከነገ ሐሙስ ጥቅምት 01/2016 ጀምሮ እስከ እሁድ ጥቅምት 04/2016 ድረስ መካሄዱ ይቀጥላል።
በዚህ ሳምንት የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ብቻ የሱፐር ስፖርት ቻናሎች ስለሚያስተላልፉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አያገኙም።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!